እንኳን አደረሣችሁ!!!
ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች፣ ለአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር አባላትና በየደረጃው የምትገኙ የማህበሩ አመራሮች እንኳን ለ2015 ዓ.ም በሰላም አደረሣችሁ።አዲሡ አመት የሠላም የጤናና የፍቅር እንዲሆን እመኛለሁ።የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር አዲሱ ዓመትን ስንቀበለው የማህበራችን 25ኛ ዓመት የምስረታ እዮቤልዮ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች የምናከብርበትን እቅድ አቅደን የምንቀሳቀስበትና የማህበሩ አባላትም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የምናረጋግጥበት በመሆኑ መላው የማህበሩ አባላት ፣ መንግስታዊ የሆኑ ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለዚሁ ስራ መሳካት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደረግልን ጥሪየን አስተላልፋለሁ።